Telegram Group & Telegram Channel
አደገኛው የመደመር ፍልስና ሚስጥር ሲገለጥ
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
"መደመር" የሚለው ቃል የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ርዕዮት እንደሆነ ተደርጎ በራሱ በብልጽግና ፓርቲ ይፋ ተደርጎዋል::
ምንም እንኩዋ መደመር የሚባል የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም በዓለማችን ባይኖርም የርዕዮቱ ፈልሳፊ ነኝ ባዩ መሪ "የፓርቲያችን የፖለቲካ መመሪያ መደመር ነው" ብሎናል - ብለውናል::
የብልጽግና ካድሬዎችም የአብይ አህመድን ቃል ተቀብለው "በመደመር መርህ አገሪቱን ወደ ብልጽግና እናሻግራለን" በማለት በመፎከርና በመፎገር ላይ ናቸው::

ነገር ግን የመደመር ጥልቅ ትርጉሙ ምንድነው? አብይ አህመድ መደመር ሲል ምን ማለቱ ነው? እንደ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን እንደ መንግስት መደመር ሲል የትኛውን አይነት መደመር ነው? የመደመር መንግስታዊ እንድምታ ምንድነው? መገለጫውስ ምን ይመስላል? ወዘተ....ለሚሉ ጥያቄዎች በቂ አሳማኝና ትክክለኛ የሆነ ምላሽ የሚሰጥ አልተገኘም::

የመደመርን ፖለቲካዊ ፍልስፍና ግልጽ አድርጎ የሚያብራራ አልተገኘም:: የመደመር ጽንሰሃሳብ ትክክለኛ ትርጉም በውል የገባው ካድሬም ሆነ የፓርቲው ደጋፊ ህዝብ የለም::
ሌላው ቀርቶ መደመር በሚለው ትልቅ መጽሃፍ ውስጥ እንኩዋ ስለ መደመር ትክክለኛ ትርጉም የሚያብራራ ትንታኔ የለም:: ቃሉ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ጋር ተያይዞ የሚጠቀስ ወይም ከኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግር ጋር ተያይዞ መፍትሄ ተብሎ መጠቀስ ያለበት ወቅታዊና አስፈላጊ ብሎም አንገብጋቢ ቃል ሆኖ የተመረጠበት ምክንያት ግልጽ አልተደረገም::

አብይ አህመድ በመደመር መጽሃፉ እንዲሁ በደፈናው "በትውልድ መንደሬ በሻሻ እያለሁ ከልጅነቴ ጀምሮ "መደመር" የሚለው ቃል ዝም ብሎ በአእምሮየ ያቃጭልብኝ ነበር" ይላል:: ቀጥሎ "የአማርኛው መዝገበቃላት ደመረ የሚለውን ቃል "ጨመረ...ይለዋል" ከማለት ውጪ ወይም ከእነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ውጪ ሌላ ስለመደመር ያብራራው ነገር የለም:: መደመር የሚለው ቃል ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ጋር ምን እንደሚያገናኘውም ግልጽ አልተደረገም::

እነዚያን ከመሳሰሉ ዓ.ነገሮች ውጪ አንዳችም ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካና ስለ መደመር አስፈላጊነትም ሆነ ስለ መደመር ጽንሰሃሳብና ስለ አሳማኝ ግልጽ ፖለቲካዊ ትርጉሙ ብሎም ስለ አፈጻጸሙ የሚያብራራ ትንታኔ የለውም!
ሆኖም መደመር የሚለው ቃል ልክ እንደ ፖለቲካ ርዕዮት ተወስዶ ዛሬ ድረስ ተደጋግሞ እየተስተጋባ የሚገኝ መንግታዊ ቃል ሆኖዋል:: በየዕለቱና በየመድረኩ "ሁላችን ስንደመር..." እየተባለ ይስተጋባል::

እርግጥ ነው ከፊሎቹ የዋህ ዜጎች "መደመር" የሚለውን ቃል ትርጉሙን ከአንድነት ጋር አያይዘው "መደመር" ማለት "አንድነት" እና "ህብረት" ማለት እንደሆነ ያስባሉ::
ገሚሱ የዋህ ዜጋ ደግሞ "መደመር" ሲባል ከለውጡ በፊት በነበረው ፖለቲካ ተቃቅሮና ተበታትኖ የሚገኘውን ብሄር-ብሄረሰብ አስማምቶና አዋህዶ በህብረትና በአንድነት አስተሳስሮ በፍቅር እንዲኖር አድርጎ መግዛት ማለት እንደሆነ ያስባሉ::
እንዲያ ቢሆን በምን እድላችን!? ነገር ግን እንደዚያ አይደለም:: ያን አይነቱን መደመር የኢትዮጵያ ህገመንግስትና የኢትዮጵያ መንግስት "አሃዳዊነት" ብለው የሚጠየፉትና የሚያወግዙት ነውና በዚያ ቀና እንድምታ ሊተረጎም አይችልም::

በብልጽግና ዘመን መደመር የሚለው ቃል በዚያ ቀና ገጽታው በቃልም ሆነ በተግባር ተተርጉሞም አላየንም:: ያን አይነቱን መደመር ወይም ያን አይነቱን የፍቅርና የአንድነት አገዛዝ ወደፊትም አናይም:: ወደፊት እንደማናይም በአጀማመራቸው ብቻ ቀድመው አረጋግጠውልናል::
ስለዚህ መደመር የሚለውን የመንግስት ቃል በዚያ ቀና ገጽታው ወስደው "ትክክለኛ ትርጉሙ እንዲያ ማለት ነው" ብለው አምነው ሊያሳምኑን አይችሉም::

ቀድሞ ነገር ህገመንግስቱ በራሱ የኢትዮጵያ ብሄርብሄረሰቦች እንዲደመሩ ዕድል አይሰጥም:: አይፈቅድምም::
ሲቀጥል በብልጽግና የተዘረጋው የአስተዳደር ስርዓት ዜጎች ከክልል ክልል በነጻነት መንቀሳቀስ የማይችሉበት አዲስ ስርዓት ነው::
ሲሰልስ ከክልሌ ውጣ የሚለው ደም አፋሳሽ ግጭት ሚሊዮኖችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ባለበት ሁኔታ ስለዚያ አይነቱ የህዝብ መደመር ማውራት አይቻልም:: ከተወራም እንደ መጥፎ ስድብና ስላቅ የሚቆጠር ነው የሚሆነው::

ሌላው ቀርቶ የክልል መንግስታት እንኩዋን እንደ ግለሰብ አመራርም ሆነ እንደ ፓርቲ እርስ በርስ አልተዳመሩም:: እርስ በርስ ካለመግባባት አልፈው (አውቀው የይምሰልም ቢሆን)በመግለጫ ሲሰዳደቡ ነው የሚያሳዩን::
የየክልሉ ህገመንግስትም ጸረ መደመር በሆኑ አንቀጾች የተሞላ ነው::
የፌደራሉ መንግስት ራሱ ጸረ መደመር ነው::ህገመንግስቱም እንደዚያው::
ከዚህ አንጻር መደመር የሚለው ቃል ኢትዮጵያ ውስጥ የገዥው ፓርቲ የፖለቲካ ርዕዮት ሊሆን አይደለም በመንግስት ደረጃ ያለምንም ግልጽ ትርጉም ሊቀነቀን የሚችልበት ምንም አይነት ኢትዮጵያዊ መነሻ መሰረትም ሆነ ይህ ነው የሚባል አሳማኝ ምክንያት የለም!

መደመር የሚለው ቃል ወይም የብልጽግና ርዕዮት በመንግስት ደረጃ ተደጋግሞ የመቀንቀኑን ያህልም በየትኛውም ዘርፍ በተግባር ደረጃ አንዲትም እርምጃ ሲኬድበት አላየንም:: ከፓርቲው በኩል በየትኛውም ዘርፍ ቢሆን ከመደመር ጋር የተያያዘ ጅምር እንቅስቃሴም ጨርሶ የለም:: ይልቁንም ህዝቦች ሲደመሩ ሳይሆን በተቃራኒ ትርጉሙ ሲቀነሱና ሲቀናነሱ ነው የምናየው::
ስለዚህ መደመር የሚለውን ቃል ከአንድነት, ከህብረትና ከህዝብ ለህዝብ ሰላማዊ ግንኙነትና ውህደት ጋር አያይዘን የምንተረጉመው ቃል አይደለም::
በዚያ እንድምታና ትርጉም እየተሰራበት ያለ ቃልም አይደለም::

ምናልባት የመደመር ጽንሰሃሳብ ከህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጋር የተያያዘ ባይሆንና በሌላ ገጽታው የሚተረጎም ሊሆንይችላል ብለን ብናስብ እንኩዋን በየትኛውም አይነት ዘርፍ ከመደመር ጋር የተያያዘ የተግባራዊነት ፍንጭ አልታየም:: "መደመር" ከህዝቦች አንድነት ውጪ በሌላ ገጽታው ማለትም ከማህበራዊ፣ከኢኮኖሚያዊ፣ከሐይማኖታዊና ከባህላዊ ሁነቶች ጋር ተያይዞ የሚተረጎም ብለን መውሰድና በዚህ ገጽታው መፍታትም አንችልም።
በአንዱ ክልል የሚገኘውን የተፈጥሮ ሃብት በሌላው ክልል ከሚገኘው የተፈጥሮ ሃብት ጋር አጣምሮና ደምሮ... ወደሚል እንድምታ አምርቶ ትክክለኛው ትርጉም ላይ መድረስ አይቻልም::
ምክንያቱም ሃብት የመቀማማት ንብረት የመዘራረፍ የመገፋፋትና የመፈነቃቀል አልፎም የ "የኔ ነው" ፖለቲካ ነው በብልጽግና ዘመን በአገሪቱ እየተራመደ ያለው::

ምናልባት ከፖለቲከኞች ወይም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር አንድነትና ውህደት ጋር ተያይዞ የሚተረጎም.... እንዳይባል ደግሞ ያለው እውነት ወደዚያ ትርጉም እንድናመራ የሚያደርግ አይደለም::

ምናልባት የፖለቲካ ርዕዮትና የአሳብ ልዩነቶችን አስማምቶ ወደ አንድ ከማምጣት ጋር ተያይዞ የሚተረጎም ነው እንዳንል....እንደዚያ እንዳልሆነ በግልጽ እናውቃለን::
በጥቅሉ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በሸፍጥ የተሞሉ ፖለቲካዊ ክንውኖችን ብቻ እንጂ አንዳችም ከመደመር ጋር የተያያዘ ፍንጭ አላየንም::

ታዲያ ምንም አይነት የመደደር ፍንጭ በሌለበት "መደመር" የሚሉን ምኑን ነው?
የመደመርን መንግስታዊ ፍቺ እና ትክክለኛ ትርጉም በየት በኩል እናግኘው? ይህን መንግስታዊ ቃል በየትኛው ገጽታው ምን ብለን እንፍታው?
አገሪቱና ህዝቡ ከመደመር ጋር ጨርሶ ግንኙነት በሌላቸው ይልቁንም ተቃራኒ

tg-me.com/ethiopianfacts/567
Create:
Last Update:

BY Amazing facts

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/ethiopianfacts/567

View MORE
Open in Telegram

Amazing facts Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Telegram Gives Up On Crypto Blockchain Project

Durov said on his Telegram channel today that the two and a half year blockchain and crypto project has been put to sleep. Ironically, after leaving Russia because the government wanted his encryption keys to his social media firm, Durov’s cryptocurrency idea lost steam because of a U.S. court. “The technology we created allowed for an open, free, decentralized exchange of value and ideas. TON had the potential to revolutionize how people store and transfer funds and information,” he wrote on his channel. “Unfortunately, a U.S. court stopped TON from happening.”

The global forecast for the Asian markets is murky following recent volatility, with crude oil prices providing support in what has been an otherwise tough month. The European markets were down and the U.S. bourses were mixed and flat and the Asian markets figure to split the difference.The TSE finished modestly lower on Friday following losses from the financial shares and property stocks.For the day, the index sank 15.09 points or 0.49 percent to finish at 3,061.35 after trading between 3,057.84 and 3,089.78. Volume was 1.39 billion shares worth 1.30 billion Singapore dollars. There were 285 decliners and 184 gainers.

Amazing facts from sa

Telegram Amazing facts
FROM USA